እስቲ ዛሬ ስለማይወራ ነገር እናውራ፡፡ዘንድሮ እዚህ አገር ስንት ሀይማኖቶች ይኖሩ ይሆን?እኔ አላውቅም እናንተ ካወቃችሁ ግን እባካችሁ አትደብቁኝ፡፡ኢትዮጵያውናችን እና ኢትዮጵያውያናትን በተመለከተ በባለፈው ቆጠራ 80 ሚሊዮን እንዳለፍን ሰምቼያለሁ፡፡በርግጥ ይሄ ቁጠር በሰው አገር ሆነው ቆጠራው ያለፋቸውን አይጨምርም፡ይሁን እንጂ ከቀጠራው ማግስት ጀምሮ ከአገር የወጡትንና አሁንም ደጅ የሚጠነትን ግን ይጨምራል።ስለዚህ ቁጥራችን ከ80 ሚሊዮን ብዙ ተቀንሶ እና ብዙ ተጨምሮ (የተወለዱትን ስንጨምርበት) ነው ማለት ነው።ከዚህ ቁጥር ዉስጥ ምንትስ ፐርሰንቱ ኦርቶዶክስ፣ምንትስ ፐርሰንቱ ወንጌላዉያን ወይም ፔነቴ ኮስታል፣ሙስሊም፣ካቶሊክ፣ባህላዊ እምነት ተከታይ ወዘተ ነው ተብሏል፡እኔም አንብቤአለሁ ሰምቼያለሁም፡፡
አሁን ግን ጥያቄዬ ይህቺ አገር የማን ነች ነው?ግን አውነት የማን ሀገር ናት-ኢትዮጵያ?ማለቴ ምንትስ ከምንትስ ብሔር ተከባብሮ የሚኖርባት፣ምንትስ ሀይማኖቶች ተዋደው፣ተፋቅረው የሚኖሩባት፣የዓለም ምሳሌ ምናምን የሚለውን የተስፈኞች ስብከት ትተን ከተጨባጩ እውነታ አንፃር ማለቴ ነው፡፡የምር ግን ወዳጆቼ በየ ቤተ ዕምነቶቻችሁ የምትሰሟቸው ስብከቶች ምን ምን ይሸታሉ?ምን ያህሎቻችሁ በቤተ ዕምነት አካባቢ የሚዘሩትን የጥላቻ ስብከቶች ሰምታችሁ አጨብጭባቸሁ ይሆን?ምን ያህሎቻችሁስ ተቆጥታችሁ ተዉ ብላችሁ ይሆን?እኔ የምለው ስንቶቻችን ነን ግን በሐይማኖት ፖለቲካ ተወስደን ከወዳጃችን የተለየን?ለመሆኑ ግን የራስን ዕውነት ለመናገር እገሌ ውሸታም ነው ማለት ግዴታ ነው እንዴ? ማለቴ በሐይማኖቶች አካባቢ?እገሊት ቆንጆ ናት ለማለት፡እገሊት ግን አስቀያሚ ናት ማለትን የሚያስገድድ ያልተፃፈ ህግ ይኖረን ይሆን እንዴ?በእውነት አሁን አሁን የሚሰሙት በሀይማኖቶች አካባቢ የሚታየው ቅጥ ያጣ ደጋፊ ለማሰባሰብ የሚደረግ እሽቅድድም፡እንዲሁም ራስን የበለጠ ኢትዮጵያዊ አድሮጎ ለማቀረብ የሚደረገው ፉክክር ማቆሚያ ቢበጅለት መልካም ነው።ማለቴ በሌላ በማንም ሳይሆን በራሳቸው በሐይማኖቶቹ፡፡ግን የምር ኢትዮጵያ የሁላችንም አይደለለችም እንዴ?ምናለ ታዲያ ለማስታወቂያ ሳይሆን የምር ተዋዳችሁ፡ተዋደን ብንኖርባት?በርግጥ አብዛኛው ምዕመን የሌላ ዕምነት ተከታይ ጐረቤቱን ይጠላል የሚል ዕምነት የለኝም፡ግን እንዲጠላ እየተደረገ ወይም እየሆነ ያለ ግን ይመስለኛል።ይሄ ደግሞ የየትኛውም ሐይማኖት መሰረታዊ የዕምነት ትምህርት የማያውቀው ተራ የሐይማኖት ፖለቲካ ይመስለኛል፡፣ነውም።ስለዚህ ሰባኪዎቻችን ፖለቲካውን ተወት አድርጉትና ስራቸሁን ስሩ፡፡ካልሆነ ኢትዮጵያን ከምናጣ እናንተ ብትቀሩብን አንመርጣለን።ኢትዮጰያ የሁላችንም ናት!
ሐሙስ 8፡07 ሰዓት ቀን
12/12/03
No comments:
Post a Comment